Amharic - አማርኛ

የፈተና መረጃን በአማርኛ ያሽከርክሩ

በቀጠሮዎ ቀን ማምጣት የሚያስፈልግዎት ነገር

በዚህ ገፅ ላይ የለማጅ ፈቃድ /Learner Permit ፈተና፣ የኣደጋ ግንዛቤ ፈተና ወይም የመንዳት ፈተና ቀጠሮ በደንበኞች ኣገልግሎት መስጫ ማእከል /Customer Service Centre ላይ ያገኛሉ።

አስተርጓሚ ወይም ተርጓሚ ስለመጠቀም

ከእንግሊዝኛ ባሻገር በሌላ ቋንቋ ከእኛ ጋር ለመነጋገር ከፈለጉ፤ ለእርዳታ ወደ አስተርጓሚ ወይም ተርጓሚ መደወል ይችላሉ።

አስተርጓሚ እንዴት መጠቀም እችላለሁ?

ቀጠሮ ሲያቀናጁ፤ ቅጽ በሚሞሉበት ጊዜ እርዳታ ከፈለጉ፤ ከቤተሰብዎ፤ ጓደኞችዎ ወይም ከ VicRoads ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።

በ VicRoads ፈተና ለመቀመጥ አስተርጓሚ ወይም እርዳታ ከፈለጉ፤ በድረገጽ VicRoads ደንበኛ አገልግሎት ማእከልን/Customer Service Centre ላይ ገብቶ ማየትና ለርስዎ ቀጠሮ ማቀናጀት እንችላለን።

የመናገርና የመስማት ችግር ላለበት

የመናገርና መስማት ጕድለት ካለብዎት፤ ሲፈተኑ የ Auslan አስተርጓሚ መጠቀም ይችላሉ።

በስልክ እኛን ለማነጋገር በ National Relay Service (External link) በኩል፡

 • ለ TTY ተጠቃሚዎች - በስልክ ቁጥር 13 36 77 በመደወል 13 11 71ን ይጠይቁ
 • ለ Speak and Listen ተጠቃሚዎች - በስልክ ቁጥር 1300 555 727 በመደወል 13 11 71ን ይጠይቁ

መንጃ ፈቃድዎን ፤ የለማጅ ፈቃድ/learner permit ወይም ሰነዶችን ስለማስተርጎም

መንጃ ፈቃድዎን ወይም የለማጅ ፈቃድ/learner permit በእንግሊዝኛ ካልሆነ፤ በNAATI ተቀባይነት ያገኘ ተርጓሚ (External link) ወይም አውስትራሊያ ውስጥ ባለ ትክክለኛ ቆንስላ የተተረጎመ መሆን አለበት።

ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል:

የታደሰ ዓለም ዓቀፍ የመንጃ ፈቃድ እንደ ውጭ ሃገር መደበኛ የመንጃ ፈቃድ እንዲተረጎም ተቀባይነት ይኖረዋል።

ዓለም ኣቀፉ የመንጃ ፈቃድ መሰጠት የሚችለው መደበኛው የመንጃ ፈቃድ በተሰጠበት ባህር ማዶ ባለው ሃገር ውስጥ ነው ።

ተቀባይነት ያላቸው ተርጓሚዎች እና ስተርጓሚዎች

ከዚህ ለሚከተሉት NAATI ተቀባይነት ላላቸው ተርጓሚዎች እንመርጣለን:

የለማጅ ፈቃድ/Learner Permit በኣካል ይፈተኑ

መርሳት የሌለብዎት:

ለዚህ በላይ የተገለጸውን ቀጠሮዎ ቅጂ ወረቀት።

የተሞላ የመንጃ ፈቃድ ወይም የለማጅ ፈቃድ/learner permit ማመልከቻ ፒዲኤፍ/ PDF (External link).

 • የማንነትዎ ኦሪጅናል ማስረጃ።
 • በቪክቶሪያ ውስጥ ስለመኖርዎ ማስረጃ።
 • በቪክቶሪያ አድራሻ ማስረጃ ከሌለዎት (ለምሳሌ፡ የባንክ ሂሳብ መግለጫ፤ የመገልገያ ክፍያ ወይም የተከራይ ውል ስምምነት)፤ በመንጃ ፈቃዱ ማመልከቻ ቅጽ ላይ የቪክቶሪያ ነዋሪ የሆነ ሰው ስለመፈረሙ ማረጋገጥ አለብዎት።
 • ውጭ አገር መንጃ ፈቃድዎ ዋናውን
 • በNAATI ተቀባይነት ባለው ተርጓኣሚ የተተረጎመ የመንጃ ፈቃድ ወይም የዓለም አቀፍ መንጃ ፈቃድ (ይህ የሚያስፈልገው የውጭ አገር መንጃ ፈቃድዎ በእንግሊዝኛ ካልሆነ ብቻ)
 • መነጸር ወይም የአይን እይታ ማስተካከያ መነጽር (ለአይን እይታ ምርመራ ማለፍ ካለብዎት)።
 • አስፈላጊ ለሆኑ የዋጋ ክፍያዎች

ለርስዎ ፈተናዎች እንዴት መዘጋጀት እንዳለብዎት

ያለዎትን ቀጠሮ ወደሌላ ጊዜ እንዴት እንደሚያስተላልፉ

ያለዎትን ቀጠሮ ወደሌላ አዲስ ጊዜ ማስተላለፍ ከፈለጉ፤ ከሚከፈል ዋጋ ጋር በ 24 ሰዓታት ማሳሰቢያ ማቅረብ ያስፈልጋል።

አንዴ ቀጠሮው ከተያዘ በኋላ መቀየር የሚችለው በቀጠሮ ያዡ ሰው ብቻ ይሆናል።

የጤና ሁኔታ ችግር አለብዎትን?

በመንዳት ችሎታዎ ላይ ችግር ሊፈጥር የሚችል፤ በሀኪም የታዘዘ መድሃኒት የሚወስዱ ወይም የጤና ችግር ካለብዎት፤ ለእኛ መናገር እንዳለብዎትና ጠቃሚ የሆነ ህክምና ሪፖርቶችን ማቅረብ አለብዎት።

ለቀጠሮዎች ደህንነቱ ስለተጠበቀ የአሰራር ሂደቶች

ለደንቦኞችንና ሰራተኞችን ጤንነትና ድህንነት ለመጠበቅ፤ ጥብቅ የጤና ሃይጂን መመሪያን በእኛ ደንበኛ አገልግሎት ማእከል/ Customer Service Centres ላይ ማስቀመጥ።

ሰዎች ጤናማ ደህና ካልሆኑ፤ ማንም ሰው በቀጠሮ መገኘት የለበትም።

በአካል የሚደረግ የአደጋ መረዳት ችሎታ ፈተና

መርሳት የሌለብዎት:

 • ከዚህ በላይ የተገለጸውን የቀጠሮዎ ወረቀት ቅጂ።
 • ይህ በወረቀት ማተም ወይም በስልክዎ ላይ ማሳየት ይቻላል።
 • የለማጅ ፈቃድዎ/learner permit ወይም የመታወቂያ ማስረጃዎ።
 • የውጭ አገር መንጃ ፈቃድዎ ዋናውን (ተግባራዊ ከሆነ)።
 • በNAATI ተቀባይነት ባለው ተርጓኣሚ የተተረጎመ የመንጃ ፈቃድ ወይም የዓለም አቀፍ መንጃ ፈቃድ (ይህ የሚያስፈልገው የውጭ አገር መንጃ ፈቃድዎ በእንግሊዝኛ ካልሆነ ብቻ)

ፈተናዎችዎ እንዴት እንደሚዘጋጁ

ለአደጋ መረዳት ችሎታ ልምምድ ፈተና ይውሰዱ

ያለዎትን ቀጠሮ ወደሌላ ጊዜ እንዴት እንደሚያስተላልፉ

ያለዎትን ቀጠሮ ወደሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ከፈለጉ፤ ከሚከፈል ዋጋ ጋር በ 24 ሰዓታት ማሳሰቢያ ማቅረብ ያስፈልጋል።

አንዴ ቀጠሮው ከተያዘ በኋላ መቀየር የሚችለው በቀጠሮ ያዡ ሰው ብቻ ይሆናል።

ለቀጠሮዎች ደህንነቱ ስለተጠበቀ የአሰራር ሂደቶች

ለደንበኞችንና ሰራተኞችን ጤንነትና ድህንነት ለመጠበቅ፤ ጥብቅ የጤና ሃይጂን መመሪያን በእኛ ደንበኛ አገልግሎት ማእከል/ Customer Service Centres ላይ ማስቀመጥ።

ሰዎች ጤናማ ደህና ካልሆኑ፤ ማንም ሰው በቀጠሮ መገኘት የለበትም።

የለመንዳት ፈተና

ለማምጣት መርሳት የሌለብዎት: / መርሳት የሌለብዎት:

 • ከዚህ በላይ የተገለጸውን የቀጠሮዎ ወረቀት ቅጂ ።
  ይህ በወረቀት ህትመት ወይም በስልክዎ ላይ ማሳየት ይቻላል።
 • የርስዎን መታወቂያ ዋናውን
 • ተስማሚ የሆነ ተሽከርካሪ።
 • የውጭ አገር መንጃ ፈቃድዎ ዋናውን (ተግባራዊ ከሆነ)።
 • በNAATI ተቀባይነት ባለው ተርጓኣሚ የተተረጎመ የመንጃ ፈቃድ ወይም የዓለም አቀፍ መንጃ ፈቃድ (ይህ የሚያስፈልገው የውጭ አገር መንጃ ፈቃድዎ በእንግሊዝኛ ካልሆነ ብቻ)
 • የርስዎ መነጽሮች ወይም የማየት ለንሥ (ለማየት ምርመራ ደረጃ ለማለፍ እና ለመንጃ ፈቃድ ፈተና ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል)።
 • አስፈላጊ ለሆኑ የዋጋ ክፍያዎች
 • እድሜዎት ከ21 ዓመት በታች ከሆነ ለተሞላ መመዝገቢያ መጽሀፍ ወይም ያጠናቀቁትን ሰዓታት በ myLearners አፕ/app አድርጎ ማስገባት ይቻላል።

ለፈተናዎችዎ እንዴት እንደሚዘጋጁ

መንዳት ፈተና ማጣሪያ ዝርዝር ያለውን ያንብቡ።

የጤና ሁኔታ ችግር አለብዎትን?

በመንዳት ችሎታዎ ላይ ችግር ሊፈጥር የሚችል፤ በሀኪም የታዘዘ መድሃኒት የሚወስዱ ወይም የጤና ችግር ካለብዎት፤ ለእኛ መናገር እንዳለብዎትና ጠቃሚ የሆነ ህክምና ሪፖርቶች ማቅረብ አለብዎት።

ለቀጠሮዎች ደህንነቱ ስለተጠበቀ የአሰራር ሂደቶች

ለደንቦኞችንና ሰራተኞችን ጤንነትና ድህንነት ለመጠበቅ፤ ጥብቅ የጤና ሃይጂን መመሪያን በእኛ ደንበኛ አገልግሎት ማእከል/ Customer Service Centres ላይ ማስቀመጥ።

ሰዎች ደህና ካልሆኑ፤ ማንም ሰው በቀጠሮ መገኘት የለበትም።

የማንነት ማስረጃ

የማንነት ሰነዶች ዓይነት

ለተሽከርካሪዎ ምዝገባ ወይም የመንጃ ፈቃድ ለማግኘት ሲመዘገቡ የማንነት መታወቂያዎን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርብዎት ይሆናል።

የርስዎን ማንነት ለመግለጽ በአካል ወደ ደንበኛ አገልግሎት ማእከል/Customer Service Centre መሄድ አለብዎት።

ያለ ትክክለኛ የሆኑ ስነዶች ለርስዎ ማመልከቻ ማጠናቀቅ አይችሉም።

ምን ዓይነት የማንነት ሰነዶች ያስፈልጉኛል?

ለማንኛውም ማመልከቻ በአብዛኛው ማቅረብ የሚኖርብዎት:

 • አንድ፤ ምድብ ሀ/Category A የማስረጃ ሰነድ (በማንነት ማስረጃውና በአመልካች መካከል ያለውን ዝምድና የሚያሳይ ማስረጃ። ለምሳሌ፡ ፓስፖርት ወይም ሙሉ የአውስትራሊያ ልደት ምስክር ወረቀት – ዋና፤ ፎቶኮፒ ወይም በተቀባይነት የተረጋገጠ ቅጂዎች ያልሆን)
 • አንድ ፤ ምድብ ለ/Category B ማስረጃ ሰነድ (ያንን መታወቂያ በማህበረሰቡ ለመጠቀምዎ ማስረጃ። ለምሳሌ፡ Medicare ወይም ባንክ ካርድ)
 • የቪክቶሪያ ነዋሪነት ማስረጃ (የርስዎ አድራሻ ምድብ ሀ/ Category A ወይም ምድብ ለ/Category B ሰነዶች ላይ የማይታይ ከሆነ)
 • ስም የቀየሩበት ማስረጃ (ምድብ ሀ/Category A ወይም ክፍል/ Category B ሰነዶች ላይ ካለዎት ስም የተለየ ከሆነ)።

የውሸት እና/ወይም አሳሳች መረጃ ወይም ሰነዶችን ማቅረብ በ Road Safety Act 1986 እና/ወይም Marine Safety Act 2010 አንቀጽ ህግ መሰረት በገንዘብ ቅጣት ወይም እስር ቤት ሊያስገባዎት ይችላል።

እርስዎ ባቀረቧቸው መረጃዎች/ሰነዶች ላይ ተመርኩዞ ማንኛውም ባለሥልጣን ወይም ተቀባይነት ባለው የተሰጠን ውሳኔ ታዲያ ውሳኔው እንደገና ሊቀየርና ተግባራዊ ላይሆን ይችላል።

ተቀባይነት ያላቸው የመለያ ሰነዶች

በርስዎ ምድብ ሀ/Category A ወይም ምድብ ለ/ Category B ሰነዶች ላይ ያለው ስም የቤተሰብዎን ስም እና ሙሉ የመጀመሪያ መጠሪያ ስምዎን እንዲሁም በተመሳሳይ አቀማመጥ መታየት ይኖርበታል።

 • ከአንድ በላይ የመጀመሪያ (የተሰጠ) ስም ካለዎት፤ የመጀመሪያ ስም በሁለቱም ሰነዶች ላይ መታየት አለበት። 
 • ከአንድ በላይ የቤተሰብ (አያት መጠሪያ) ስም ካለዎት፤ ሁሉም ስሞች በሁለቱም ሰነዶች ላይ መታየት አለበት።

ለሌላ ሰው ወይም ኩባንያ ወክሎ ስለመሥራት

የሆነን ሰው በመወከል የሌላን ሰው ተሽከርካሪ ለማስመዝገብ በተወካይነት ለመስራት የሚያስችል ስልጣን መስጫ ቅጽAuthority to Act as an Agent form [PDF 253 Kb] (External link) ላይ መፈረም ይኖርብወታል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት ወደ አንድን ሰው ወክሎ ለመመዝገብ/Register on behalf of someone else ገብቶ ማየት።

በምድብ ሀ ሰነዶች

ለቤተሰብዎ ስም፤ የመጀመሪያ ስም እና ለርስዎ ልደት ቀን ምድብ እንዲታይ ክፍል/Category A ሰነዶች dያስፈልጋል።

ሰነዶች ወቅታዊ መሆን እንዳለባቸው ወይም ጊዜው ያለፈበት ከሁለት ዓመታት በላይ መሆን የለበትም።

ተቀባይነት ያለው ያገኘ በምድብ ሀ ሰነዶች

 • የአውስትራሊያ ፎቶ ያለው መንጃ ፈቃድ ወይም ፎቶ ያለው የለማጅ ፈቃድ/learner permit ካርድ።
 • ፎቶ ያለው የቪክቶሪያ የባህር ሀይል ፈቃድ ካርድ።
 • ፎቶ ያለው የቪክቶሪያ የጦር መሳሪያ ፈቃድ
 • ፎቶ ያለው የቪክቶሪያ የደህንነት ጠባቂ/የሰው ክምችን ተቆጣጣሪ ካርድ።
 • የአውስትራሊያ ፓስፖርት።
 • የውጭ አገር ፓስፖርት (ሁለት ዓመታት በላይ የሆነው ከወቅታዊ የአውስትራሊያ ቪዛ ጋር ተያይዞ ከቀረበ ተቀባይነት አለው።
 • በ Passport Office በኩል የተሰጠ የማንነት ምስክር ወረቀት
 • በ Passport Office በኩል በስምምነት የተሰጠ የጉዞ ሰነድ።
 • በ Passport Office በኩል የተሰጠ የማንነት መለያ ሰነድ (አብዛኛው ወደ ኖርፎርክ ደሴት/Norfolk Island ለሚጓዙት ይሰጣል)
 • የአውስትራሊያ ፖሊስ ሀይል መኮንን ፎቶ ያለው መታወቂያ ካርድ።
 • በDepartment of Foreign Affairs and Trade የተሰጠ ፎቶ ያለው የኮንሱላር መታወቂያ ካርድ
 • በልደት፣ ሞት እና ጋብቻ/Births, Deaths and Marriages ምዝገባ የተሰጠ ሙሉ የአውስትራሊያ ልደት ምስክር ወረቀት (ማሳሰቢያ: ተቀንጭቦ የወጣ ልደት እና የማስታወሻ ልደት ምስክር ወረቀቶች ተቀባይነት የላቸውም)።
 • የአውስትራሊያ ተወላጅ ወይም የዜግነት ምስክር ወረቀት፤ ወይም ወደ አውስትራሊያ ለመጓዝ የተሰጡ ሰነዶች ወይም ImmiCard (እስከ 2 ዓመታት ጊዜው ለሚያበቃ) በDepartment of Immigration and Citizenship ወይም በ Passport Office በኩል ይሰጣል።
 • የኒው ሳውዝ ወልስ/NSW ፎቶ ያለው ካርድ (ከቀን 14 ታህሳስ/December 2008 ጀምሮ በ NSW RMS ይሰጣል)።
 • የልደት ካርድ (ከነሐሴ/August 2008 በፊት በ NSW RMS ይሰጣል)።
 • እባክዎ ያስታውሱ: የውሸት እና/ወይም አሳሳች መረጃ ወይም ሰነዶችን ማቅረብ በ Road Safety Act 1986 እና/ወይም Marine Safety Act 2010 አንቀጽ ህግ መሰረት በገንዘብ ቅጣት ወይም እስር ቤት ሊያስገባዎት ይችላል።
 • እርስዎ ባቀረቧቸው መረጃዎች/ሰነዶች ላይ ተመርኩዞ ማንኛውም ባለሥልጣን ወይም ተቀባይነት ባለው የተሰጠን ውሳኔ ታዲያ ውሳኔው እንደገና ሊቀየርና ተግባራዊ ላይሆን ይችላል።

በምድብ ለ ሰነዶች

ከዚህ የሚከተሉት ሰነዶች ውስጥ ወቅታዊ የሆነ ኣንደኛው ሰነድ።

 • ለአስተዳደር ግዛት ወይንም ፈደራል መንግሥት ተቀጣሪን ፎቶ ያለው መታወቂያ/ID ካርድ።
 • Medicare ካርድ።
 • Department of Veterans Affairs ካርድ
 • Pensioner Concession ካርድ
 • በ Commonwealth የተሰጠ ወቅታዊ ፈቃድ ማስገኛ ካርድ።
 • የተማሪ መታወቂያ ካርድ።
 • ከባንክ፤ የህንፃ ማሕበር ወይም ክረዲት ማሕበር ለተሰጠ ማንኛውም የአውስትራሊያ ወይም የውጭ አገር ክረዲት ካርድ።
 • ከህጻናት ጋር ስለመስራት የሚደረግ ማጣሪያ/Working with Children Check ካርድ።
 • የአውስትራሊያ የእድሜ ማስረጃ ካርድ።
 • የአውስትራሊያ Keypass ካርድ።
 • የ Australian Defence Force ፎቶ ያለው መታወቂያ ካርድ (ሲቪልያን ሰራተኞችን ያላካተተ)።

ወይም

 • ከነዚህ ሰነዶች ውስጥ ከአንድ ዓመት በላይ ያልሆነው (በመሳሪያ ላይ ኤለትሮኒክስ ጽሁፋዊ መግለጫ (ለምሳሌ፡ ሞባይል ስልክ ወይም ታብለት ላፕቶፕ) እንዲሁም በኢንተርኔት የታተመ ጽሁፋዊ መግለጫ ወረቀት ተቀባይነት ማግኘት ይችላል):
 • የባንክ የቁጥር ደብተር ወይም ባንክ አካውንት ጽሁፋዊ መግለጫ የተቋማትን አርማ ወይም ማህተም የሚያሳይ።
 • ተለፎን፤ ጋዝ ወይም ኤለትሪክሲትይ ለክፍያ መጠየቂያ የተቋማትን አርማ ወይም ማህተም ለሚያሳይ።
 • ከ ATO, Centrelink, ባንክ እና Medicare ደብዳቤዎች የተቋማትን አርማ ወይም ማህተም የሚያሳይ።

ወይም

 • ከነዚህ ሰነዶች ውስጥ ከአንድ ዓመት በላይ ያልሆነው: የውሃ መጠን ቀረጥ፤ የምክር ቤት ቀረጥ/council rates ወይም ለመሪት ዋጋ ግምገማ ማሳሰቢያ
 • በኤለክትሮኒካል ምርጫ ምዝገባ ካርድ ወይም ለምዝገባ ሌላ ማስረጃ
 • ከታጠቀ ጦር አገልግሎቶች መውጫ ደብዳቤ
 • ወቅታዊ የሆነ Victorian Driving Authority ፎቶ ያለው መታወቂያ ካርድ ይሆናል።

ምድብ ሐ ሰነዶች - የአድራሻ ለውጥ

የቪክቶሪያ መኖሪያን አድራሻዎት የማይታይ ከሆነ ወይም ከርስዎ ምድብ ሀ/Category A ወይም ምድብ ለ/ Category B የማስረጃ ሰነዶች ለየት ያለ ከሆነ ከሚከተሉት ሰነዶች ውስጥ አንዱ ያስፈልግዎታል:

 • አሁን ያሉበትን አድራሻ ለሚያሳይ የሽያጭ፤ ኩንትራት ወይም የተከራይ ሰነድ ውል
 • በቅርቡ የታደሰ የመንጃ ፈቃድ ወይም ለተሽከርካሪ ምዝገባ
 • Australian Taxation Office Assessment (ባለፈው ወይም በአሁን ፋይናሻል ዓመት)
 • አሁን ያሉበትን አድራሻ የሚያሳይ የተለያዩ ምድብ/Category A ወይም ምድብ ለ/ Category B ሰነዶች።
 • አሁንም የቪክቶሪያ ነዋሪ መሆንዎን ማስረጃ ማቅረብ ካልቻሉ፤ ለሚከተለው ያካተተ የምስክርነት ጽሁፋዊ መረጃን ማቅረብ አለብዎት:
 • ይህም ለቪክቶሪያ የመንጃ ፈቃድ የያዘው ሰው ለ 12 ወራት ወይም ከዚያ በላይ በሚያውቀው የተፈረመ እና የመስካሪውን ስም፣ መንጃ ፈቃድ ቁጥርና ፊርማን ያካተተ ይሆናል።

ይህ ጽሁፋዊ መግለጫ በለማጅ ፈቃድ/learner permit ወይም በመንጃ ፈቃድ ማመልከቻ ቅጽ ላይ ማቅረብ ይቻላል።

ምድብ መ ሰነዶች - የስም ለውጥ

ስምዎት በምድብ Category A እና በክፍል/ Category B ዶኩመንት ማስረጃ ለየት ያለ ከሆነ ከሚከተሉት ሰነዶች ውስጥ አንዱ ያስፈልግዎታል።

 • አውስትራሊያ ውስጥ በልደት፣ ሞት እና ጋብቻ/Births, Deaths and Marriages ምዝገባ የተሰጠ የጋብቻ ምስክር ወረቀት።
 • ከትዳር የፍት ወረቀት (የተቀየረን ስም የሚያሳይ)።
 • Deed Poll (በቪክቶሪያ ውስጥ ከህዳር/November 1986 ዓ.ም በፊት የተሰጠ)።
 • የስም መቀየር ምስክር ወረቀት/Change of name Certificate (በቪክቶሪያ ውስጥ ከህዳር/November 1986 ዓ.ም በኋላ የተሰጠ)።

ለኩባንያ የማንነት መለያ ሰነዶች

ተሽከርካሪ በኩባንያ የተመዘገበ/registered ከሆነ ከሚከተሉት አንዱ ያስፈልጋል:

 • የአውስትራሊያ ኩባንያ ቁጥር/Australian Company Number (ACN)
  • ይህ ምዝገባ/registered በሚካሄድበት ጊዜ እያንዳንዱ የአውስትራሊያ ኩባንያ ዘጠኝ ዲጂት ያለው የተለየ ቁጥር የአውስትራሊያ ኩባንያ ቁጥር/Austrlian Company Number ተብሎ ለሚታወቅ መለያ ቁጥር ያገኛሉ።
   ይህ መለያ ቁጥር በእያንዳንዱ ለሚሰጥ ህዝባዊ ሰነድ ላይ በኩባንያው* ተወካይ በኩል ተፈርሞ ወይም ተጽፎ ይቀርባል፤ ወይም
 • የምዝገባ ምስክር ወረቀት/Certificate of Registration
  • በተጨማሪም ለእያንዳንዱ የተመዘገበ/ registered ኩባንያ በ ACN, ASIC በኩል የምዝገባ ምስክር ወረቀት/Certificate of Registration ይቀርባል፤ ወይም
 • የውህደት ምስክር ወረቀት/Certificate of Incorporation

* የአውስትራሊያ ንግድ ሥራ ቁጥር/Australian Business Number (ABN) ከ ACN የተለየ ነው።

ABN አስራ አንድ ዲጂታል ቁጥር ያለው ብቸኛ ቁጥር ሲሆን ይህም ከAustralian Taxation Office እና ከሌሎች መንግሥታዊ ድርጅቶች ጋር የንግድ ሥራ ለመደራደር የሚጠቅም መለያ ቁጥር ነው።

አውስትራሊያ ውስጥ የንግድ ስራዎች ለማካሄድ የሚፈቀድላቸው በተመዘገቡ/Registered ኩባንያዎች እና ንግድ አውታሮች ለABN ማመልከት ይችላሉ።

ማስታወሻ: /strong> የአውስትራሊያ ንግድ ሥራ ቁጥሮች/Australian Business Numbers (ABNs) ድርጅቱ የተወሃደ ህጋዊ አካል /incorporated body ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።

ኩባንያን ወክሎ መስራት

ለሚከተሉትን ማቅረብ አለብዎት:

 • የምድብ ሀ/Category A ወይም ለ/ B ሰነዶች የመለያ ማስረጃ
 • ከኩባንያው ዳረክቶር ወይም ከውህደት ኩባንያው አርማ ያለበት ባለስልጣን ዋናውን ደብዳቤ።
  ከዚህ በታች ያሉትን መረጃ ማካተት አለበት:
  • አርማ ያለበት ደብዳቤ ላይ ሙሉ የኩባንያው ስም እና አድራሻ
  • የአውስትራሊያ ንግድ ሥራ ቁጥሮች/Australian Company Number (ACN) ወይም በህግ ለተቋቋመ ድርጅት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/Certificate of Incorporation
  • ኩባንያውን ወክሎ የሚንቀሳቀስ ግለሰብ ስም
  • ኩባንያውን ወክሎ ለመንቀሳቀስ ዝርዝር የሥራ እንቅስቃሴዎች (ለምሳሌ፡ ለምዝገባ እደሳ)።

ኩባንያው አርማ ያለው ደብዳቤ ከሌለው ወካይነት ለመስራት የሚያስችል ስልጣን መስጫ ቅጽ/Authority to Act as an Agent form [PDF 253 Kb] (External link) መጠቀም ይችላል።

ለሚከተሉት ሥራዎች አንድን ሰው ወክሎ ማካሄድ አይቻልምም

 • ፈተና መውሰድ
 • በየቀኑ ሥራ መግዛት
 • ፎቶ መነሳት።

Was this page helpful?

 

Please tell us why (but don't leave your personal details here - message us if you need help or have questions).